🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች እና የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 25 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየውን አራተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለጉብኝት የመጡትን እንግዶች በመቀበል፣ በኤክስፖው የቀረቡ የአምራች ኢንዱስትሪ ውጤቶችንና በንቅናቄው የተመዘገቡ ስኬቶችን አስጎብኝተዋል።
በኤክስፖው ላይ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራቾች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡
微信扫一扫 立即联系我们