登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን እየጎበኙ ነው

发布:5/7/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እየጎበኙ ነው፡፡

የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።

በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል።

በተጨማሪም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል፡፡


በዚህም የጉባኤው አካል የሆነውን ጉብኝት የጀመሩ ሲሆን፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚመጥነውን ሥራዎቿን ታስጎበኛለች፡፡

ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ጉባዔ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል።

የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ሀላፊነት የሚሰማቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር፣ ትብብርን ለመፍጠርና አዲስ አበባን የባህልና የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们