登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤቶችን በማስፋት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ማፋጠን ያስፈልጋል

发布:5/6/2026 阅读:2

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 26/2018 (ኢዜአ)፦በሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ማፋጠን እንደሚያስፈልግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ገምግሟል።


የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በሪፖርታቸው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በዘንድሮው በጀት ዓመት 10 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ የሚያስችል ስኬት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በተሰራው ሥራም በታኅሳስ 2018 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የዋጋ ግሽበቱን ዘጠኝ ነጥብ ሰባት በመቶ በማድረስ ወደ አንድ አሃዝ ማውረድ መቻሉን አመልክተው፤ የመጋቢት ወርም ወደ ዘጠኝ ነጥብ አራት በመቶ መውረዱን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት መንግስት ከብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ብድር አልወሰደም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ የሚወሰደው ብድር እንዲቆም መደረጉም የዋጋ ንረትን እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል።

በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ አማካኝነት ኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ እፎይታ እንድታገኝ ስኬታማ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ድርድር መደረጉን ጠቅሰዋል።

በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ በጥብቅ የፊስካል ፖሊሲ ቁጥጥርና የቁጠባ ዲሲፕሊን በመመራቱ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ ዕድገት የምታስመዘግብ ሀገር እያደረጋት መሆኑን አንስተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም፤ የሚኒስቴሩን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ በዋጋ ግሽበት፣ የዕዳ ሽግሽግና ተያያዥ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በምላሻቸው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ በደመወዝ ጭማሪ፣ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ፣ የምግብ ዘይትና መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ መንግስት ድጎማ እያደረገ ነው ብለዋል።

በሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በተደረጉ ስኬታማ ድርድሮችም ኢትዮጵያ ከጣሊያንና ፈረንሳይ ጋር የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት መፈረሟን አስረድተዋል።

ከቻይና ጋርም የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት መፈረም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ያለው ድርድር መቀጠሉን ገልጸዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፤ ሪፖርቱ ቀጣይነት ያለው ዕድገት መኖሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በዋጋ ንረትን፣ ዕዳ ሽግሽግ፣ በወጪና ገቢ ንግድ አፈፃጸም የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ውጤቶችን በማስፋት ዕድገትን ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们