登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

ኮርፖሬሽኑ በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ገበያዎች ለመሰማራት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል 

发布:5/6/2026 阅读:3

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 26/2018(ኢዜአ)፦ ኮርፖሬሽኑ ባስቀመጠው ራዕይ መሠረት በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ገበያዎች ለመሰማራት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ተግባር ምዕራፍ መሸጋገሩን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ረሻድ ከማል ገለጹ።


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ በቤት ግንባታ ዘርፍ መሰማራት የሚያስችለውን ታሪካዊ ስምምነት ተፈራርሟል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በመሪዎች ደረጃ የጋራ የልማት ትብብር በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ስምምነት መደረሱን ተከትሎ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መካከከል በቤት ልማት ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈጽሟል፡፡


በኢትዮጵያ ፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና በደቡብ ሱዳን የማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መንግሥት መካከል የተደረገው ይህ የመግባቢያ ሰነድ፣ በጁባ ከተማ በቤቶች ልማትና አስተዳደር ዘርፎች በጋራ መሥራት የሚያስችል መሠረት ጥሏል ነው ያለው ኮርፖሬሽኑ።

ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት መንግሥት አስተዳዳሪ ኢማኑኤል አዲል በይፋ መፈረማቸውን ኢዜአ ከኮርፖሬሽኑ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

ይህ ውል ኮርፖሬሽኑ ያለውን የረጅም ጊዜ ልምድና የቴክኒክ አቅም በመጠቀም በጁባ ከተማ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሕንፃዎችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲያከናውን ሰፊ መንገድ እንደሚከፍትም ተመላክቷል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፣ ኮርፖሬሽኑ ባስቀመጠው ራዕይ መሠረት በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ገበያዎች ለመሰማራት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል።


ኮርፖሬሽኑ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውና አዋጭ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።

በደቡብ ሱዳን የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት መንግሥት አስተዳዳሪ ኢማኑኤል አዲል በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ፈጣን የከተሞች ለውጥ ለመላው አፍሪካውያን ተምሳሌት መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታም በርካታ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል።

በተለይም በቤት ልማት ዘርፍ በኢትዮጵያ ያለውን ተሞክሮ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመሆን በጁባ ከተማና በግዛቱ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።


ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር፣ ኮርፖሬሽኑ በቤት አስተዳደርና ልማት ያለውን ውጤታማ ተሞክሮ ለግዛቱ ባለሙያዎች የሚያጋራበትንና የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን የሚሰጥበትን ዕድል ያመቻቻል ብለዋል።

የስምምነቱን አፈጻጸም በቅርበት የሚከታተል፣ ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነዶችን የሚያዘጋጅና አጋዥ የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚያመነጭ የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቋቋም መወሰኑም ተመላክቷል።

ይህ ስምምነት የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገሩ በላይ፣ የኢትዮጵያን የቤቶች ልማት ተሞክሮ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለማስፋፋት ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们