登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በዞኑ ሰላምን በማጽናት የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ይጠናከራሉ

发布:5/6/2026 阅读:3

🔇Unmute

ደብረ ማርቆስ፣ሚያዚያ 26/2018 (ኢዜአ)፦በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰላምን በማጽናት የማህበረሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ።‎

በዞኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ የሚመክር መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሄዷል።

‌‎በመድረኩም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሰላምን በማስፈን ለልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በቀሪ ወራትም ተጨማሪ ስራዎችን በማከናወን የበለጠ ስኬት ለማስመዝገብ ርብርብ እንደሚደረግ ጠቅሰው፤ ‎መድረኩም በስራ አፈፃፀም የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ድክመቶችን ለማረም ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ደምስ አለኸኝ በበኩላቸው፤ በዞኑ የሰፈነው ሰላም የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማከናወን ማስቻሉን ጠቁመዋል።

በዞኑ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማፋጠን ተግባር ህብረተሰቡን ባሳተፈ አግባብ እየተከናወነ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።

በዞኑ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ለተሻሻሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች ትኩረት መሰጠቱን ያነሱት ደግሞ የዞኑ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ንጋቱ ናቸው።

በዚህም በ2017/18 የምርት ዘመን የሰብል ምርታማነትን በሄክታር ከ35 ወደ 38 ኩንታል ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

በመኸር ወቅቱ ከለማው ከ640 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ጠቅሰው፤ በመስኖ ልማቱም እስካሁን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል ብለዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ውሃ ስራዎች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ከፍያለው ሙላቴ፤ በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እንዲጠናከሩ አሳስበዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们