登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ቀጣናዊ ደኅንነትን ለማስጠበቅ እና ለጋራ ዕድገት ወሳኝ ነው

发布:5/6/2026 阅读:2

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 26/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር፣ ለጋራ ተጠቃሚነትና ለቀጣናው ደኅንነት መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ምሁራን ገለጹ።

ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሁራን እንደገለጹት፤ የሀገሪቱ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የህልውና እና የቀጣናዊ እድገት ጉዳይ ነው።

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ተከትላ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የሚበረታታ ነው።


የባህር በር ማግኘት የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስረድተው፤ ለወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ፍትሐዊ፣ ሕጋዊ፣ ታሪካዊና መልክዓ-ምድራዊ እውነታን መሰረት ያደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ቀጣናዊ ትስስርን በማጎልበት፣ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑንና ለቀጣናው ሀገራት ዘላቂ ሰላምና የጋራ ልማት የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ሲሳይ ደመቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የባህር በር ከሸቀጥ ዝውውር ባለፈ የሃሳብ፣ የቴክኖሎጂና የቱሪዝም ፍሰትን በማሳለጥ በኩል ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል።


የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር፣ ለጠንካራ ደህንነት፣ ለኢኮኖሚና ለቴክኖሎጂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የሎጂስቲክስ ወጪን በመቀነስ የገቢና ወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን፣ ለቀጣናው ደህንነት መጠበቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们