登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

ኢትዮጵያ በኤ አይ ዘርፍ ያላትን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው

发布:5/6/2026 阅读:2

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 26/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) ዘርፍ ያላትን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና ከእሑድ ኤ አይ ስቱዲዮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኤ አይ ሙዚቃ ውድድር ተካሂዷል፡፡

ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደሉት ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) ዘርፍ ያላትን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት አሁን ላይ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ችግሮች የሚፈቱበት ቁልፍ መሳሪያ እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡


ኤ አይ የሰው ልጅን የማሰብ፣ የመገንዘብ፣ የማመዛዘን፣ የማቀድ፣ የመማርና ቋንቋን የመረዳት አቅምን በማሳደግ የተለያዩ ተግባራትን በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በጥበብና መዝናኛው ዘርፍ ያለውን አስተዋጽኦ ይበልጥ ለማጠናከር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት አዲስ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን ለችግሮች አዲስ የመፍትሄ ሃሳብ ማመላከቻ መንገድ በመሆን በዘርፉ ይዘቶችን በፍጥነት ለማዘጋጀት አማራጭ ሃሳብ ይዞ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡

ተቋማቸው ኤ አይ ቴክኖሎጂን በሚገባ የተረዳ እና ለበጎ አላማ የሚጠቀም የሰው ሃይል ለማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡


የኤ አይ ሙዚቃ ውድድሩ የዚሁ ሥራ አካል መሆኑን ጠቁመው ይህም ቴክኖሎጂው በጥበብ ዘርፍ ያለውን አቅም ከማሳየት ባለፈ በኢትዮጵያ ታሪክ የቴክኖሎጂና ጥበብን ጥምረት መግለጽ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡

ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የኤ አይ ሙዚቃ ውድድር በጎ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ ትግበራን በማበረታታት ወጣቶች ቴክኖሎጂውን በሃላፊነትና በሥነ ምግባር እንዲጠቀሙ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ውድድሩ በሙዚቃ ባለሙያዎች እና በዘርፉ ሥራ ፈጣሪዎች መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የይዘት ፈጠራ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች መኖራቸውን መረዳት እንደተቻለ ጠቁመው በሒደቱ የተገኘው ውጤት አበረታች እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们