登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልማት እድገትና ማንሰራራት የሚደነቅ ነው

发布:5/6/2026 阅读:3

🔇Unmute

ጅማ ፤ ሚያዝያ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልማት እድገትና ማንሰራራት የሚደነቅ መሆኑን በካናዳ ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁር አሊ አስጋሪ (ፕ/ር) ተናገሩ።

ኢትዮጵያ የዲጂታል መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ እውን ለማድረግ እየተጋች መሆኑ ይታወቃል።

ከዲጂታል ልማትና የቴክኖሎጂ እድገት በተጓዳኝ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል በብዛት የማፍራት ስራ እየተከናወነም ይገኛል።

በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ዜጎችን በነፃ ተጠቃሚ የሚያደርገው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናም የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው ።

በኢትዮጵያ እየተከናወነ ላለው የዲጂታል ልማት በተለይም ደግሞ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን እና ፈጠራን ለማስፋፋት የሚደረገው ጥረት በላቀ ውጤት እየተገለጠ እና የበርካቶችን እውቅና እያገኘ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው መሾማቸውም የጥረቱ ስኬት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም በተመለከተ ተሞክሯቸውን ለማካፈል ከተገኙት በካናዳ ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁር አሊ አስጋሪ (ፕ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልማት እድገትና ማንሰራራት ለሌሎች ሀገራት በጥሩ በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልማትና ተግባራዊ እንቅስቃሴዋ አስደናቂ መሆኑን በማንሳት በአጭር ጊዜ የመጣው ውጤት እና የታየው ስኬት ለቀጣይም ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ሆኗል ብለዋል።

ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት በተጓዳኝ በዘርፉ ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚደረገው የተቀናጀ ጥረትም የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል።

በኢትዮጵያም የተቋማት ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትልቅ ትርጉም የሚኖረው መሆኑን አንስተው ለዚህም ጠንካራ መሰረት እያኖረች መሆኑን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

ከዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በነበራቸው ውይይት የተረዱትም ይህንኑ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ በዘርፉ ልማትና ትግበራ ትልቅ ተስፋ የሰነቀችና ወደፊት እየተራመደች ያለች ሀገር መሆኗን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም እየሰራች መሆኑ ደግሞ በቀጣይ ለዘርፉ ልማት ሌላ እመርታ የሚያመጣ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በዲጂታል ልማት የያዘችውን ተግባራዊ እቅድ እያሳካች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂክ ትግበራን በስኬት አጠናቅቃ ሌላ የዲጂታል 2030 ስትራቴጂክ እቅድ ነድፋ በመተግበር ላይ መሆኗ ይታወቃል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们