登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በክልሉ የበጀት አስተዳደርና አጠቃቀምን በማዘመን በህዝብ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠቱ ተግባር ይጠናከራል

发布:4/30/2026 阅读:3

🔇Unmute

ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የበጀት አስተዳደርና አጠቃቀምን በማዘመን በህዝብ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ።

በፕሮግራም በጀት አሰራርና አተገባበር ዙሪያ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተወካይ አቶ ኡቶው ኡኮት በመድረኩ ላይ እንዳሉት ፤በክልሉ እየተመዘገበ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስቀጠል የበጀት አስተዳደርና አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ።

ለዚህም ክልሉ ያለውን ውስን በጀት በአግባቡ በማስተዳደር በህዝብ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ ክልሉ ባለፉት ዓመታት ያለውን ውስን በጀት ስራ ላይ በማዋል የህዝቡን የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም የፋይናንስ አሰራርና አጠቃቀም ሂደቱን ይበልጥ በማዘመን የክልሉን ልማትና እድገት ለማፋጠን በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት እቅድና በጀት ከውጤት ጋር በማስተሳሰር ቀጣይነት ያለውና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝግብ የሚያስችል’’የፕሮግራም በጀት’’ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩንም ገልጸዋል።

በመሆኑም እንደ ሀገር ለተጀመረው የፕሮግራም በጀት ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ስኬታማነት የክልሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተወካዩ አስገንዝበዋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ኡማን አሙሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፤ባለፉት ዓመታት ሲተገበር የቆየው የበጀት አጠቃቀምና አሰራር በርካታ ለውጦች የታዩበት ነው ብለዋል።

ቀልጠፋና ውጤታማ የበጀት አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር ውስንነቶች እንደነበሩ አመልክተው ይሕንን ለመቀየር ይሰራል ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ የሚተገበረው የፕሮግራም በጀት ቀደም ሲል የነበሩ ክፍተቶችን እንደሚያስቀር ጠቁመው ለተግባራዊነቱ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们