登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላምና እድገትን በምርምር ማገዝ አለባቸው

发布:4/30/2026 阅读:3

🔇Unmute

ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለማምጣት ያላቸውን አቅም ማጠናከር እንዳለባቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ገለፁ።

"ቀጣናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዓለምአቀፍ የምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው በቪዲዮ ኮንፍረንስ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በጥናትና ምርምር መደግፍ አለባቸው።


ለዚህም ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አስገንዝበዋል።

በተለይም ሀገረሰባዊ እውቀቶችን በምርምር በማስደገፍ በቀጣናው ሀገራትበዘመናዊ አስተዳድር ሥርአት ውስጥ የሚካተቱበትን አቅም መፍጠር ላይ ይበልጥ ማተኮር አለባቸው ብለዋል።


የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) በበኩላቸውዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለሀገርና ለቀጣናዊ ችግሮች መፍትሄ የሚሆኑ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማበርከቱን ጠቅሰዋል።


የአየር ንብረት ለውጥ በቀጣናው እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ ለመከላከል ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያከናወነችው ተግባር በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢንስቲትዩት (GGGI) ተወካይ ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ ናቸው።

የአፍሪካ ሕብረት በ2063 የሀይል፣ የውሀ ሀብትና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት የኢትዮጵያን ልምድ ሊቀስም ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።


በካናዳ የዩርክ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሮፌሰር አሊ አስጋሪ ኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂ አቅርቦትና ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እድገት የሰጠችው ትኩረት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በምርምር ጉባኤው በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ፣ በጤና፣ በትምህርትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥናቶች በተመራማሪዎች፣ በፖሊሲ አውጪዎችና ባለሙያዎች እየቀረቡ ነው።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们