登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሰራሩን በማዘመን በታላቅ የሽግግር ሂደት ላይ ይገኛል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

发布:4/30/2026 阅读:3

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማዘመን በታላቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እያከናወነ የሚገኘውን የሪፎርም ሥራዎች ጎብኝተዋል።


ከንቲባዋ በጉብኝቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከተማ አስተዳደሩ ለተቋም ግንባታ የሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

ተቋማት ቀጣይነት ያለው ሥራ እንዲሰሩና የአገልግሎት አሰጣጣቸውም ዘላቂ እንዲሆን የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ትልቅ ማሣያ ነው ብለዋል።

ተቋሙ ከቅጣት ይልቅ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት ላይ እየሰራ መሆኑን አብራርተው፤ የደንብ ጥሰት ተፈጽሞ ሲገኝ ብቻ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ በቴክኖሎጂ ራሱን በማዘመንና በመረጃ ላይ በመመስረት ሕግና ሥርዓትን ወደ ማስከበር መሸጋገሩን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ባለስልጣኑ ወረቀት አልባ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የከተማዋ የስማርት ሲቲ ግንባታ አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

አሰራሩን በሞባይል መተግበሪያም ጭምር በመስጠት ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ መጀመሩንም ተናግረዋል።


ማህብረሰቡ የደንብ ጥሰት ሲፈጸም ካለበት ቦታ ሆኖ ጥቆማ የሚሰጥበት ዘመናዊ አሰራር መዘርጋቱንም ጠቅሰዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሰራሩን በማዘመን በታላቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们