登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በክልሉ ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ ከ169 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር እየተሰራጨ ነው 

发布:4/29/2026 阅读:2

🔇Unmute

ባህርዳር ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ለ2018/19 የምርት ዘመን ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ ከ169 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን የክልሉ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን አስታወቀ።

‎የባለስልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም ልየው ለኢዜአ እንደገለፁት፤ጥራትና ደህንነቱ በላብራቶሪ የተረጋገጠ ዘር ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ የክልሉን ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።


በዚህም ለ2018/2019 የምርት ዘመን ጥቅም ላይ የሚውል ከ169 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጤፍና ሌሎች የሰብል ዘር ጥራትና ደህንነት በላብራቶሪ በማረጋገጥ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል።

የዘር ጥራትና ቁጥጥር ስራው የተካሄደው በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ፣ በግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ በዩኒየኖችና በግል ዘር አብዢዎች የቀረበውን መሆኑን ጠቅሰዋል።


የዘር ጥራትና ደህንነቱ በላብራቶሪ ተፈትሾና ተረጋግጦ በህብረት ስራ ማህበራትና በዘር አብዢዎች አማካኝነት ለአርሶ አደሩ የሚሰራጨው ምርጥ ዘርም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩም ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ ዘር ገዝቶ በመጠቀም ምርታማነቱን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነቱን ለማረጋገጥ እንዲሰራ መክረዋል።


‎የክልሉ ግብርና ቢሮ የዘር ብዜት ባለሙያ አቶ ጥላዬ ሞገሴ እንዳሉት ከባለስልጣኑ ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ የሚቀርበውን ዘር ጥራት በማረጋገጥ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት እየተሰራ ነው።

በዚህም አርሶ አደሩ በህገወጥ መንገድ ዘርን ገዝቶ እንዳይጠቀም ተከታታይ ትምህርት በባለሙያዎች እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በዘንድሮው የመኸር አዝመራ ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር እንደሚሸፈን ከክልሉ ግብርና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们