登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በዞኑ ቋሚ ፍራፍሬን በኩታ ገጠም በማልማት አርሶ አደሩን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

发布:4/29/2026 阅读:3

🔇Unmute

ደሴ ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ወሎ ዞን በኩታገጠም ቋሚ ፍራፍሬን በማልማት የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በዞኑ እስከ ሐምሌ 30/2018 የሚዘልቅ 900 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም እርሻ ፍራፍሬን ለማልማት የሚያስችል የችግኝ ተከላ ዘመቻ ተጀምሯል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ዞኑ የፍራፍሬ ችግኝ ተከላውን የሚያካሔደው ተስማሚ ስነ-ምህዳርና የአየር ንብረት ባላቸው አምስት ወረዳዎች ነው።

በዚህ የዘመቻ ስራ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ሙዝ፣ ብርቱካንና ሌሎች ቋሚ የፍራፍሬ ችግኞችን የመትከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።


የችግኝ ተከላው በተሁለደሬ፣ በአምባሰል፣ በቃሉ፣ በወረባቦና በአርጎባ ብሔረሰብ ወረዳዎች እየተከናወነ ነው።

ይህም በዘልማድና በተበታተነ አግባብ የሚካሔዱ የፍራፍሬ ልማት ስራዎችን በማስቀረት የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

በአጭር ጊዜ ምርት የሚሰጥ፣ በሽታን የሚከላከልና ምርታማ የፍራፍሬ ችግኝ ለአርሶ አደሩ እየቀረበለት እንደሚገኝም ነው የገለጹት።

በተለይ በሎጎ ሀይቅ ሪዞርት ዙሪያ የለማው የፍራፍሬ ልማት ውጤታማ በመሆኑ በአርሶ አደሩ ዘንድ ከፍተኛ መነሳሳትን መፍጠሩን ነው የገለጹት።


በተሁለደሬ ወረዳ የ012 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሰይድ ፈንታ እንዳሉት ፣ በሎጎ ሀይቅ ሪዞርት ዙሪያ የለማው የፍራፍሬ ተክል በአጭር ጊዜ ምርት ሲሰጥ መመልከቴ መነሳሳትን ፈጥሮብኛል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም በግማሽ ሄክታር ማሳቸው ላይ ከ100 በላይ የተሻሻሉ የሙዝ ችግኞትን መትከላቸውን ገልጸዋል።


የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መሀመድ አደም በበኩላቸው፣ በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መሰረትም ቋሚ የሆኑ ፍራፍሬዎችን እያለሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በጫት ተሸፍኖ የነበረውን ሩብ ሄክታር መሬታቸውን በመመንጠርም ፓፓያና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞችን እየተከሉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሉባባ ሰይድ ናቸው።


በደቡብ ወሎ ዞን በመጪው ክረምት በ3 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们