登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

ያገኘነውን ልምድና እውቀት ተጠቅመን ማህበራት የተሻለ ቁመና ላይ እንዲደርሱ ኃላፊነታችንን እንወጣለን-ሰልጣኞች

发布:4/29/2026 阅读:3

🔇Unmute

ኮምቦልቻ ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ያገኘነውን ልምድና እውቀት ተጠቅመን የሕብረት ሥራ ማህበራት የተሻለ ቁመና ላይ እንዲደርሱኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ በኮምቦልቻ የሕብረት ስራ ሪፎርም ስልጠና ተሳታፊዎች ገለፁ።

የኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን “ቀበሌ የመድረስ ምዕራፍ” በሚል መሪ ሃሳብ በኮምቦልቻ ሲያካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የሕብረት ሥራ ሪፎርም የንቅናቄ መድረክና ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።


የስልጠናው ተሳታፊዎች ፤ ከስልጠናው ያገኘነውን እውቀትና ልምድ ተጠቅመን የህብረት ስራ ማህበራት የተሻለ ቁመና ላይ ሆነው ኢኮኖሚውን እንዲያነቃቁ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከል አቶ ሰለሞን እንቁዬ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ የጀመረው ሪፎርም ባለሙያውን በማነቃቃት ገበያውን እያረጋጋ ኢኮኖሚውንም እያሳደገ ይገኛል።


ስልጠናው ህብረት ስራ ማህበራትን ለማጠናከር፣ ለማዘመን፣ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማሻሻል፣ የፈጠራ ስራዎችንና አዳዲስ ሀሳቦችን በማዋሀድ በሪፎርሙ የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠልና ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።

በዚህም ያገኘነውን ልምድና እውቀት ተጠቅመን ማህበራት የተሻለ ቁመና ላይ እንዲደርሱና ኢኮኖሚውን እንዲያነቃቁ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።

ሌላኛዋ ሰልጣኝ ማርታ ጌቱ በበኩላቸው፣ ስልጠናው የህብረት ስራ ማህበራትን እንቅስቃሴ በማጎልበት ለውጤት እንዲበቃ ሚናው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።


በተለይ ማህበራትን በአዲስ በማደራጀት፣ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ ካፒታላቸውን በማሳደግና የቁጠባ ባህላቸውን በማጠናከር ገበያውን እንዲያረጋጉና ኢኮኖሚውን እንዲያነቃቁ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል።

ማህበራት የተሻለ ቁመና ላይ እንዲደርሱ በተከናወኑ ተግባራት የተገኘውን አበረታት ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት እንሰራለን፣ ለዚህም ከስልጠናው እውቀትና ልምድ አግኝተናል ያሉት ደግሞ አቶ መሀመድ ሆላ ናቸው።


በተለይ ማህበራትን ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር በማጣጣም የበለጠ ለውጤት እንዲበቁ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው በኮምቦልቻ ከተማ ተዘዋውረን በመጎብኘት የልምድ ለውውጥም ማድረግ ችለናል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ አምባዬ ወልዴ በበኩላቸው፤ ህብረት ስራ ማህበራትን በማጠናከር፣ በማዘመን፣ ካፒታላቸውን በማሳደግ፣ ትስስር እንዲፈጥሩና የላቀ ደረጃ እንዲደርሱ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


ለዚህም አዲስ ሪፎርም ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን አስታውሰው ኢኮኖሚውን በማነቃቃትና ገበያውን በማረጋጋት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።

የበለጠ ለማጠናከርና ባለሙያውንም ለማነቃቃት በተለያየ ዙር ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው በኮምቦልቻ ሲካሄድ የቆየው ስልጠናም ዛሬ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ከሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው ስልጠናና የንቅናቄ መድረክ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራሮች እንዲሁም የአማራና የአፋር ክልል የቀበሌ ህብረት ሥራ ማህበራት ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们