登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን በመጭው የምርት ዘመን ከ412 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በዘር ይሸፈናል

发布:4/29/2026 阅读:3

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 20/2018 (ኢዜአ)፡- በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን በመጭው የመኸር ወቅት 412 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የሰብል ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ አንዱዓለም አያሌው ለኢዜአ እንዳሉት፤ ለመጭው የመኸር ወቅት 412 ሺህ 480 ሔክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ17 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው።


ከዚህ ውስጥም 70 በመቶው በኩታ ገጠም የሚለማ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ከ85 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት ለ2ኛ ጊዜ ደጋግሞ በማረስ ለዘር ዝግጁ ተደርጓል ብለዋል።

ከሚያስፈልገው 840 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እስካሁን ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነውን በማስገባት ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ከ5 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር ተሰራጨቷል ያሉት ቡድን መሪው፤ በመስመር መዝራትና ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን መጠቀም ላይ በማተኮር እንደሚሰራም አስረድተዋል።

በየደረጃው ያለው የግብርና ባለሙያ እና አመራሩ አርሶ አደሩን በመደገፍና በማማከር የሚጠበቀውን የምርት እድገት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ምአስገንዝበዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们