登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንግልትና አላስፈላጊ ወጪን አስቀርቶልናል - ተገልጋዮች

发布:4/29/2026 阅读:3

🔇Unmute

ሆሳዕና፤ ሚያዝያ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንግልት እና ያልተገባ ወጪን እንዳስቀረላቸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሆሳዕና ከተማ ተገልጋዮች ገለፁ፡፡

በማዕከሉ አገልግሎት በማግኘት ላይ የነበሩት አቶ ዮናስ ሴራሞ ለኢዜአ እንደገለፁት ፤የገቢ ግብር ጉዳይ ላይ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ማዕከሉ እንደመጡና ባጠረ ጊዜም የሚፈልጉትን ፈጽመው ለመመለስ መቻላቸውን ነው የሚገልጹት።


የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተገልጋይን ከአላስፈላጊ ከሆነ እንግልትና ወጪ እንደሚታደግ በተግባር ያረጋገጡ መሆኑንም ተናግረዋል።

የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ለማውጣት ወደ ማዕከሉ የመጣው ወጣት ሞላልኝ ታምራት በወቅቱ አገልግሎቱን ማግኘቱን እናማዕከሉ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይታይ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር በመቅረፍ ለማሕበረሰቡ አስፈላጊ የሆነ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ነው የገለጸው።



በማዕከሉ የተገልጋዩን ክብር የጠበቀ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኝቷ እንዳስደሰታት የምትገልፀው ደግሞ ወጣት በረከት ዱቲሶ ናት፡፡


በፋይዳ መታወቂያዋ ላይ ያጋጠማትን የስም ስህተት በአጭር ጊዜ ማስተካከል ችያለሁ ብላለች።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ሻሜቦ ማዕከሉ በስምንት ተቋማት 27 አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡


እስካሁን ድረስ ከ 20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት መስጠት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

በከተሞች በመሬት ዘርፍ የሚሰጡና ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ አዳዲስ 48 አገልግሎቶች ተለይተዉ በማዕከሉ ውስጥ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻልም ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们