登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

አዲስ ገቢር ነበብ የፖለቲካ ኢኮኖሚ

发布:4/24/2026 阅读:1

🔇Unmute

‎ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበረው ግትር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አስተሳሰብ ተላቃ፣ ትኩረቱን በተግባራዊ አፈጻጸም ላይ ያደረገ አዲስ ገቢር ነበብ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እይታ የተቃኘ የፖሊሲ ማዕቀፍ መከተል ከጀመረች ሰነባብታለች።

‎ይኅው አዲስ አቅጣጫ፤ ሀገሪቱ ለወቅታዊ የዓለምና የሀገር ውስጥ ነባራዊ ሁኔታዎች ምላሽ የሚሰጡ ተግባራዊ መፍትሄዎችን እንድትቀይስ አስችሏታል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የሪፎርም ጉዞ፣ መንግሥትንና የግሉን ዘርፍ እንደ ወሳኝ አጋር በማየት፣ በውጤትና በውጤታማነት ላይ የተገነባ አዲስ የመንግሥት የሥራ ባህልን ተቋማዊ አድርጓል።

‎‎በዚህ ገቢር ነበብ እይታ አማካኝነት፣ በሚከተሉት ስምንት ቁልፍ ምሰሶዎች ወሳኝ ስኬቶች ተመዝግበዋል፦

‎• በኢኮኖሚ ዕይታ ረገድ፦ የመንግሥትን ሚና ዳግም በመተርጎም፣ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና ዘርፈ-ብዙ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎች አማካኝነት የገበያ ውድድር እንዲሰፍንና የኢኮኖሚ አቅም እንዲጎለብት ተደርጓል።

‎• በአማራጭ ፋይናንስ ዘርፍ፦ የካፒታል ገበያ ልማትን በማብሰር፣ የመንግሥትና የግል አጋርነትን በማጠናከር እና ዘመናዊ የገንዘብ ገበያ በመፍጠር የሀገሪቱን የፋይናንስ አማራጮች ማሳደግ ተችሏል።

‎• በኢኮኖሚ አመራር በኩል፦ በመደበኛ ክትትልና ግምገማ፣ በማክሮ ኮሚቴና በዘርፍ ካውንስሎች የተቀናጀ አሰራር አማካኝነት የገንዘብ ፖሊሲና የፕሮጀክቶች አስተዳደር ይበልጥ ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆን ተደርጓል።

‎• የግል ዘርፍ ሚናን በማሳደግ፦ የግሉ ዘርፍ ከማህበራዊ ኃላፊነት ባለፈ የኢኮኖሚው መሪና ዋና ሞተር እንዲሆን በማድረግ እንደ ትልቅ የልማት አጋር እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።

‎• በልማት አጋርነትና ንግድ ትስስር ፦ የብድር ሽግሽግና አዲስ ፋይናንስን በማረጋገጥ፣ ለዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት የሚደረገውን ሂደት በማፋጠንና የAfCFTA ትግበራን ውጤታማ በማድረግ የሀገሪቱ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ተወዳዳሪነት ከፍ ብሏል።

‎• በማህበራዊ ደህንነት ረገድ፦ አካታችነትን፣ ተደራሽነትንና ጥራትን መሠረት ያደረገ የሰው ተኮር ድጋፍ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ማድረግ ተችሏል።

‎• በፍትሃዊ የመሰረተ ልማት ስርዓት ፦ የአካባቢ ጸጋን መሠረት ያደረገ፣ በግልጽ የሕግ ማዕቀፍ የሚመራና ያለፉ የፍትሃዊነት ክፍተቶችን የሚሞላ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥርዓት ተግባራዊ ሆኗል።

‎• በስርዓት ግንባታ በኩል፦ ብሔራዊ አካታች ምክክርን በማካሄድ፣ በፍትህና በሲቪል ሰርቪስ ዘርፎች ሪፎርም በማድረግ እንዲሁም የዲሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

#PMOEthiopia

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们