登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የኢትዮጵያ ታምርት የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል

发布:4/24/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡

የጎዳና ላይ ሩጫውን በተመለከተ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታምርት የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አስተባባሪ አብዱልፈታህ የሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ታምርት የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

የሩጫ ውድድሩ ገቢ ምርትን በመተካት የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስፖርት አልባሳትን ማስተዋወቅ እና የማምረት አቅማቸውን ማሳየትን አላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ዜጎች የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህል እንዲያሳድጉ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መሆኑንም አመላክተዋል።

ውድድሩ አዲስ አበባ ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሀብት ለማስተዋወቅ ተጨማሪ እድል እንደሚፈጥርም እንዲሁ።

በውድድሩ ከ15 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ እና ከእነዚህ ውስጥ 500 የሚሆኑት አትሌቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህ ውድድር በሴቶችና በወንዶች 1ኛ ለሚወጡ 550 ሺህ ብር፣ 2ኛ ደረጃን ለሚይዙ 300 ሺህ ብር እንዲሁም በ3ኛነት ለሚያጠናቅቁ ደግሞ 200 ሺህ ብር እንደሚበረከት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክቶሬት ተወካይ ጊዜ አድነው በበኩላቸው፤ የጎዳና ላይ ሩጫው ለአትሌቶች አዲስ የውድድር እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们