登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የደዋጨፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ቋሚ የሆኑ የፍራፍሬ ተክሎችን ለማልማት የችግኝ ተከላ ስራ ጀምረዋል

发布:4/23/2026 阅读:1

🔇Unmute

ደሴ፤ ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦ቋሚ የሆኑ የፍራፍሬ ተክሎችን ለማልማት የችግኝ ተከላ ስራ መጀመራቸውንበኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የደዋጨፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ ከሁለት ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም የፍራፍሬ ልማት ማረስ መጀመሩን አስታውቋል።

በዞኑ በደዋጨፋ ወረዳ የሸክላ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መሀመድ ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ አንድ ሄክታር ማሳቸውን በኩታ ገጠም በሙዝ ተክል በማልማት የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ ነው።


እስካሁን ከ800 በላይ የተሻሻሉ የሙዝ ችግኞችን መትከላቸውን ጠቁመው፣ ችግኞቹ ጸድቀው ተገቢውን ምርት መስጠት እንዲችሉ እንክብካቤ እያደረጉ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

በአካባቢው ዓመቱን ሙሉ የሚፈስ ወንዝ ቢኖርም እስካሁን እንዳልተጠቀሙበት ጠቁመው የተከሉት የሙዝ ችግኝ በዘጠኝ ወር ምርት የሚሰጥ በመሆኑ ተጠቃሚነታችንን የሚያረጋግጥ እንደሚሆንም እምነት አለኝ ብለዋል።

ሌላው የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ ወጣት እንድሪስ ሁሴን በበኩሉ፤በሁለት ሔክታር መሬት ላይ መንግስት በነጻ ያቀረበላቸውን የተሻሻለ የፍራፍሬ ችግኝ በኩታ ገጠም እርሻ ማሳቸው እያለሙ እንደሚገኙ ተናግሯል።


ከፍራፍሬ ተክሎቹ ውስጥ ሙዝና ፓፓያን እያለማ ሲሆን እስካሁን አንድ ሺህ 600 የሙዝ ችግኞችን ለመትከል ችያለሁ ነው ያለው።

በአካባቢው ቀድመው በፍራፍሬ ልማት ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ መሆናቸውን በማየት ወደ ሙዝ ልማቱ መግባታቸውን ገልጿል።

ግማሽ ሄክታር ማሳዬን በፍራፍሬ ለማልማት የሙዝ ችግኞችን መትከል ጀምሪያለሁ ያሉት ደግሞ በወረዳው የገርቢ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አህመድ ኡመር ናቸው።


መንግስት በአጭር ጊዜ ምርት የሚሰጥ፣ ምርታማና በሽታን የሚከላከል የሙዝ ዝርያ በነጻ ያቀረበልን በመሆኑ ተገቢውን እንክብካቤ አድርገን የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን እየሰራን ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው፣ በዞኑ ፍራፍሬ በስፋት በማልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከሁለት ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት በኩታገጠም እርሻ ፍራፍሬን የማልማት ሥራ መጀመሩንም ነው ያስረዱት።

ልማቱን ለማሳለጥም ለአርሶ አደሩ በአጭር ጊዜ ምርት የሚሰጥ፣ በሽታን የሚከላከልና ምርታማ የሆኑ የሙዝ ችግኝ በነጻ ማቅረብ መቻሉን አመላክተዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们