登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በክልሉ የሚሰበሰበው ግብር ለከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

发布:4/23/2026 阅读:1

🔇Unmute

ባህርዳር ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በክልሉ የሚሰበሰበው ግብር ለከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) ገለጹ።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በባህር ዳር ከተማ እየተካሔደ ያለውን የኮሪደርና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ዛሬ ጎብኝተዋል።


የቢሮ ኃላፊው መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ የሚሰበሰበው ግብር የከተሞችንና የገጠሩን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማቶችን ለማሳለጥ እየዋለ ነው።

ለዚህም በባህር ዳር ከተማ የተገነቡት የኮሪደር ልማት፣ መሶብ አንድ ማዕከል፣ ሰፋፊ የአስፋልት መንገዶች፣ የአረንጓዴ ልማትና ሌሎች መዝናኛዎች ማረጋገጫ ናቸው ብለዋል።

የተገነቡት የመሰረት ልማት ስራዎችም የከተሞቹን ገጽታ በመቀየርና የህብረተሰቡን አኗኗር በማሻሻል ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ መሆናቸውንም ነው ያመለከቱት።

በቀጣይም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ለክልሉ እድገት ለማዋል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት።

የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው፤በከተማዋ የኮሪደርና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መካሔዳቸው የቱሪዝምና የኢንዱስትሪ ፍሰት እንዲጨመር አድርጓል።


ልማትን በተገቢው መንገድ ለማከናወን ገቢን አሟጦ መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ አመልክተው ለዚህም የተቋሙ ሰራተኞች ይበልጥ በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

በጉብኝቱ የተሳተፉት ወይዘሮ ትዕግስት ዘሪሁን እንደገለጹት፤ ሰራተኛው የልማት ፕሮጀክቶችን እንዲጎበኝ መደረጉ ገቢን አሟጦ ከመሰብሰብ አኳያ በላቀ ተነሳሽነት እንዲሰራ የሚያደርግ ነው።


በከተማ እየተካሔዱ ያሉት የልማት ፕሮጀክቶች ከሕብረተሰቡ የሚሰበሰበው ገቢ ማሕበረሰቡን የመሰረተ ልማት ተጠቀሚ ለሚደረጉ የልማት ስራዎች መዋሉን የሚያረጋግጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራትም 69 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ማዋል መቻሉንም ነው ያስገነዘቡት።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们