登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ኢትዮጵያን ለንግድና ለኢንቨስትመንት የሚመርጧት ሃገር አድርጓታል - ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

发布:4/22/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ኢትዮጵያን ለንግድና ለኢንቨስትመንት አጋርነት የምትመረጥ ሀገር እንዳደረጓት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የ100 ቀናት ግምገማና የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ሚኒስትሯ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ መሪዎች ኢትዮጵያን መጎብኘት ችለዋል።


ይህም የተከናወነው የለውጥ ስራ እና በዚህ አማካኝነትም እየመጣ ያለው ለውጥ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ እንደሆነ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ከእርዳታ ይልቅ ለንግድና ለኢንቨስትመንት አጋርነት የምትመረጥ እንዲሁም የመወዳደር አቅሟ ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን ገልጸዋል።

ራሳችንን የገለጽንበት መንገድ ኢትዮጵያ ከተረጂነት እይታ ይልቅ ሉአላዊነትን ያረጋገጠች እርዳታ ቢያስፈልጋት እንኳን በራሷ ማሳካት የምትችል መሆኗንም አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከዓለም መዛመድ የምትፈልግው ለንግድና ለኢንቨስትመንት ነው የሚለው ትርክት የራሱን ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

የተሰሩ ስራዎችና የልማት ውጤቶች ማድረግ የመቻል አቅምን በማሳየት ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ያላትን የግንኙነት ገጽታ የቀየሩ መሆኑን አስረድተዋል።

ከአየር ንብረት ለውጥ ዲፕሎማሲና ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ መሪነት አኳያም ከፍ ያሉ ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በምታራምደው ፖሊሲና አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በዓየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በተግባር ያከናወነቻቸው ስራዎች በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃም ያሳየችው የመሪነት ሚና ተጠቃሽ ሃገር እንዳደረጋትም አስረድተዋል።

የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ መቻሏም የራሱን ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ዓለም አቀፉን የዓየር ንብረት ጉባኤ (COP 32 ) እንድታስተናግድ መመረጥ መቻሏም የዚሁ ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ #ሃገራዊ_ለውጥ

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们