🔇Unmute
አሶሳ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦የህብረት ስራ ማህበራት የተቀላጠፈ ግብይት እንዲኖር ለማድረግ፤ የካፒታል መጠንን ለመጨመር እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት መሆናቸውንየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሬትና ህብረት ስራ ማደራጃ ቢሮ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛውን ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ በአሶሳ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሬትና ህብረት ስራ ማደራጃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ካሚል ሀመድ፤ የህብረት ስራ ማህበራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ብዝሃ ኢኮኖሚን መሠረት ያደረገ ሪፎርም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የህብረት ስራ ማህበራት የተቀላጠፈ ግብይት እንዲኖር ለማድረግ የካፒታል መጠንን ለመጨመር እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት መሆናቸውን ገልጸዋል።
ንቅናቄው በክልሉ የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት አደረጃጀታቸውን በማዘመንና የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን የህብረት ስራ ግብይት መሪ ስራ አስፈጻሚ ንጋቱ ቶላ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ንቅናቄው የህብረት ስራ ማህበራት ተግባር እና ተልዕኳቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ንቅናቄው የህብረት ስራ ማህበራት ወደ ኢንዱስትሪ ምርት እንዲገቡ እንዲሁም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል እንደሆነ አንስተዋል።
በመጀመሪያው ዙር የንቅናቄ መድረክ ተሳታፊ የነበሩ የህብረት ስራ ማህበራት አመቻቾች በአደረጃጀት ደካማ የነበሩ ማህበራት እንዲጠናከሩ እና በኢኮኖሚ አቅማቸው ጠንካራ እንዲሆኑ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
ለስምንት ቀናት የሚቆየው የንቅናቄ መድረክም በህብረት ሥራ ሪፎርም ፅንሰ-ሐሳቦች እና በዘመናዊ የህብረት ስራ አሠራሮች እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩርም አስታውቀዋል።
በንቅናቄው ላይ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
微信扫一扫 立即联系我们