登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶች ለአፍሪካውያን 'እኛም እንችላለን' የሚል ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ናቸው

发布:4/22/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ የመሰረተ ልማት ስኬቶች ለአፍሪካውያን 'እኛም እንችላለን' የሚል ተነሳሽነትን የሚፈጥሩና የሚያኮሩ ናቸው ሲሉ ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች ገለጹ።

በአዲስ አበባ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታዩት ግዙፍ ለውጦች ከተማዋን የአፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የንግድ መዲናነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ ናቸው።

ለአብነትም የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችና የአገልግሎት ዘርፍ ሽግግርና ሌሎች የተገኙ ውጤቶች ይጠቀሳሉ።


15ኛው የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሴክሪቴሪያት የቴክኒካል ኮሚቴ አህጉራዊ ስብሰባ በቅርቡ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በጉባኤው የተሳተፉ ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፥ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማእከል መሆኗን በተግባር ማሳየት ተችሏል።

በተጨማሪም አዲስ አበባ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ለልማት አጀንዳዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር በኩል ያሳየችው ብቃት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የሚመጥን የአረንጓዴ ልማት፣ ዘመናዊነትና ውበት እንዲሁም ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የተከናወኑ ስራዎች በቅርብ ዓመታት የተገኙ ለውጦች የሚደነቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ይህም ለአፍሪካውያን "እኛም እንችላለን" የሚል ተነሳሽነትን የሚፈጥርና የሚያኮራ ስራ ነው ብለዋል።


ከዛምቢያ የመጡት ማርያ ዲየን ፔሪ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ ከአመታት በፊት ይኖሩ እንደነበረ ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ባዩት ሁሉን አቀፍ ለውጦች መደነቃቸውን ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አጀንዳዎች ላይ የሚካሄዱ ጉባኤዎችን በማስተናገድ ጉልህ ሚና እያበረከተች እንደምትገኝ ይገልጻሉ።

በመሰረተ ልማት ግንባታና በሎጂስቲክስ አገልግሎትም አስደናቂ ለውጦች መገኘታቸውንም ጠቁመዋል።

ሌላው ከዛምቢያ የጉባኤው ተሳታፊ ቺጋጉራ ሚቲ በአሁኗ አዲስ አበባ እና ቀደም ሲል በነበረችው ከተማ መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው ብለዋል።


አዲስ አበባ አህጉራዊ አቅምን የአፍሪካ ባለሙያዎች ትልቅ ችሎታ የምታሳይ ምሳሌ መሆኗንም አክለዋል።

ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን በማስፋፋት የንግድ እና የዲፕሎማሲ ስራዎችን በፈጣን ሁኔታ ማከናወን የሚያስችሉ ስርዓቶች መዘርጋታቸውንም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ሰዎች ራእይና ቁርጠኝነት ካላቸው ተአምር መስራት እንደሚቻል የምታሳይ ምሳሌ ናት ሲሉም ተናግረዋል።

ከቡሩንዲ የመጣችው ሊስ ኤስታ ካራኩቲማ በበኩሏ አዲስ አበባ በዲፕሎማሲ፣ በቴክኖሎጂ፣ በመሰረተ ልማትና በሌሎች ዘርፎች ለአፍሪካ ሀገራት አርአያ ናት ብላለች።


በኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ልምድ ማዳበርንና ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት የተሰሩ ስራዎች በአጭር ጊዜ የተገኙ ውጤቶች ተነሳሽነትን እንደሚፈጥሩም ገልጻለች።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们