登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የህብረት ስራ ማህበራትን ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስትራቴጂ ጋር በማጣጣም የበለጠ ውጤታማ ማድረግ ተችሏል

发布:4/22/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዳማ ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የህብረት ስራ ማህበራትን ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስትራቴጂ ጋር በማጣጣም የበለጠ ውጤታማ ማድረግ መቻሉን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን "ወደ ቀበሌ መድረስ" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው 2ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ሪፎርም ንቅናቄ መድረክ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል።


መድረኩን በንግግር የከፈቱት በምክር ቤቱ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ እንደገለጹት፤ በሀገራችን ከሪፎርሙ በፊት በርካታ ህብረት ስራ ማህበራት ቢኖሩም፣ አብዛኞቹ ራሳቸውን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ያስማሙ አልነበሩም።

በዚህም ምክንያት ዘርፉ ለአባላቱም ሆነ በአጠቃላይ ለሀገር እድገት ሊወጣ የሚገባውን ዘርፈ-ብዙ ጥቅም ሳያስገኝ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቅት የማህበራቱን ሚና ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስትራቴጂ ጋር ለማጣጣም መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ ውጤትም እየተገኘ መጥቷል ብለዋል።

መንግስት ለሪፎርሙ ስኬታማነት የ"ስትሪንግ ኮሚቴ" በማደራጀት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሰለሞን፤ በአሁኑ ወቅት የማሻሻያ ህግጋት ተዘጋጅተው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙና ለዘርፉ የሚሆን ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል።

የህብረት ስራ ኮሚሽን "ቀበሌ መድረስ" በሚል መርህ አደራጆችን ያሳተፈ ንቅናቄ መጀመሩ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው፤ ህብረት ስራ ማህበራት የሀገር ኢኮኖሚ ማሳለጫ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።


በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት በጥናት ላይ ተመስርቶ በተደረገ ሪፎርም 31 ሺህ በላይ ማህበራት በስም ብቻ የሚታወቁና አድራሻ የሌላቸው መሆናቸው መለየቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም 5 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ራሳቸውን ችለው መቆም ስለማይችሉ ከሌሎች ጋር እንዲዋሀዱ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 4 ሺህ የቀበሌ አደራጅ ባለሙያዎች በስልጠናው እየተሳተፉ መሆኑን ጠቅሰው፤ ስልጠናው በተለያዩ ማዕከላት ለተከታታይ ስምንት ቀናት ይሰጣል ብለዋል።

በመድረኮቹም የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና የብልፅግና ጉዞ መሰረት ያደረጉ የዘርፉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们