🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግር ያላትን የላቀ ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ማካፈላቸውን ገልጸዋል።
በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ ተሞክሮ የተቀዱ ከፍ ያሉ ሀሳቦች መነሳታቸውን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
微信扫一扫 立即联系我们