登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በኮምቦልቻ ከተማ የተገነቡ የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ተመርቀው ስራ ጀመሩ

发布:5/12/2026 阅读:1

🔇Unmute

ኮምቦልቻ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፡-በኮምቦልቻ ከተማ ከ877 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ተመርቀው ሥራ ጀመሩ።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ እና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ እንደገለፁት፣ በከተማው የኢንዲስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ባለፉት ጥቂት ወራትም ስድስት ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት የገቡ ሲሆን ፤ዛሬ የተመረቁትን ጨምሮ አጠቃላይ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዳሉም ገልፀዋል።

ኢንዱስትሪዎቹ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በመተካትና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረት ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ እያገዙ ነው ብለዋል።


በዛሬ እለት ተመርቀው ወደ ማምረት የተሸጋገሩት የምግብ ዘይትና ቆርቆር ማምረቻ ፋብሪካዎችም ለአካባቢው ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ በበኩላቸው፤ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፉ ለከተማዋ ፈጣን እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።

የከተማዋ ለወደብ ቅርብ መሆን፣ የአየር ትራንስፖርት መኖር፣ አስተማማኝ ሰላም መረጋገጡና ሌሎችም ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም ዘርፉን ለማሳደግ በተቀናጀ አግባብ በተደረገ ድጋፍና ክትትል ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ነው ያስገነዘቡት።

የ"ሁዳ" ምግብ ዘይት ፋብሪካ ባለቤት ተወካይ አቶ ሀሰን ሰይድ በበኩላቸው፣ በ127 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ፋብሪካው በቀን 50 ሺህ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም እንዳለው ተናግረዋል።


መንግስት ለግል ባለሃብቶችና ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ውጤታማ እንዳደረጋቸው አንስተው፤ ፋብሪካው ከ250 ለሚበልጡ ዜጎችም የስራ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

ሌላው "የኡሙል ኸይር" ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለቤት አቶ መሀመድ አብደላ በበኩላቸው፤ ከ750 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጭ የተገነባው ፋብሪካው በቀን ከ21 ሺህ በላይ ቆርቆሮ እያመረተ ነው ብለዋል።

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባም በቀን 40 ሺህ ቆርቆሮ የማምረት አቅም እንዳለውም ገልጸዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们