🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ በ2018 በጀት ዓመት በአስር ወራት ከ600 ቢሊየን ብር በላይ ጥቅል ገቢ መሰብሰቡን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) አስታወቁ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃጸምን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙኅን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፤ የኢትዮጵያን ፋይናንስ የማመንጨት አቅም ለማሳደግ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 598 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር ተናግረዋል።
ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ሥርዓት በመዘርጋት፣ ፈጣን ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከርና ኮንትሮባንድን በመከላከል ከዕቅዱ በላይ መፈፀም እንደተቻለ ገልጸዋል።
በዚህም በአስር ወራት ከታቀደው በላይ 600 ነጥብ 23 ቢሊየን ብር በላይ ጥቅል ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።
የዘንድሮው አፈፃጸም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው አንጻር የ75 ነጥብ 29 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።
የአመራሮችንና ሙያተኞችን አቅም በመገንባትና በየሩብ ዓመቱ በመገምገም የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነትን ማሳደግ እንደተቻለ ጠቁመዋል።
በድንገተኛ ፍተሻ ስራዎች ተለይተው ከተፈተሹ ሰነዶች ወደ ገቢ የሚቀየር ሁለት ነጥብ 864 ቢሊየን ብር መገኘቱንም አንስተዋል።
በበጀት ዓመቱ አስር ወራት በሕገ-ወጥ ንግድ፣ ማጭበርበርና ኮንትሮባንድ ተግባራትን በመከላከል በኩል ህብረተሰቡን በማስተባበር፣ የውስጥ አቅምን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ከ279 ነጥብ 855 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን እንደተቻለ ገልጸዋል።
ይኸውም ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 54 ነጥብ 86 በመቶ ድርሻ እንዳለው ጨምረው ተናግረዋል።
微信扫一扫 立即联系我们