登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በክልሉ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው

发布:5/12/2026 阅读:1

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ከ81 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።


የቢሮው የአፈር ለምነት ማሻሻያ ባለሙያ አምሳሉ አድማስ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊየን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ከተዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ግማሽ ያህሉን በ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ በመበተን ከአፈር ጋር የማዋሃድ ሥራ መሰራቱንና በቀሪው ማዳበሪያም ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ማዳበሪያ ሳይንሳዊ አሰራሩን ተከትሎ በጥራት ከተዘጋጀ የአፈር ስነ ህይወታዊ ዘዴን በማሻሻል ለምነቱን በቀላሉ ለመመለስና ምርታማነትን ለማሳደገ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንምአስረድተዋል።

ባለፈው ዓመት በክልሉ ከ71 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት በማዘጋጀት ጥቅም ላይ መዋሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们