登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በክልሉ በመጪው ክረምት ከ10 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በአቮካዶ ተክል ይሸፈናል

发布:5/12/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዳማ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ በክልሉ በመጪው ክረምት በሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ገለፀ።

በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ የአቮካዶ ልማት ኢኒሼቲቭን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።

በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል።

በተለይ ለወጪ ንግድ የሚሆን አቮካዶ ልማትን ለማሳደግና ምርትና ምርታማነቱን ማሳደግ ለሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው በሁሉም የክልሉ ዞኖች፣ ከተሞችና ወረዳዎች በክላስተርና በመደበኛነት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们