登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

በርካታ ሰዎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ማሸጋገር ያስቻለው የከተማ ግብርና

发布:5/12/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማ ግብርና ዘርፍ በተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት በርካቶችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ማሸጋገር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።

ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የከተማ ግብርና ቤተሰብ መፍጠር መቻሉንም ጠቁሟል፡፡

በከተማ ግብርና እየተሳተፉ የሚገኙ ዜጎች በበኩላቸው፤ በዘርፉ በመሰማራታቸው ከዕለታዊ ፍጆታ ባለፈ ሌሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻላቸውን ይናገራሉ።

በከተማ ግብርና የተሰማሩ ዜጎች በበኩላቸው፤ ከራሳቸው ፍጆታ ባለፈ ለሌሎች ማኅበረሰብ ክፍሎች ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የከተማ ግብርና ስትራቴጂዎች ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ፣ ዜጎች በራሳቸው አቅም ምግብን ማምረት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየና የሥራ ባህልን የቀየረ ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው፡፡

ይህ የተቀናጀ ጥረት ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በምግብ ራስን ለመቻልና ከድህነት ለመውጣት ለጀመረችው ጉዞ እንደ ትልቅ ስኬት የሚወሰድ ነው።


የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማ ግብርና በተከናወኑ ተግባራት ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመለወጥ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ቀደም ሲል የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም በከተማ ግብርና አይቻልም የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት በመቀየር፣ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የከተማ ግብርና ተጠቃሚ ቤተሰቦችን መፍጠር ማቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በተመሣሣይ ከሁለት ሺህ ሰባት መቶ በላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተቀናጀ ሁኔታ በከተማ ግብርና ላይ እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አብራርተዋል።

በመዲናዋ በከተማ ግብርና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ዜጎች ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

በከተማ ግብርና በአነስተኛ ቦታ ላይ በማምረት ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት ማቅረብ መጀመሩንም ጠቁመዋል።

በከተማ ግብርና እየተሳተፉ የሚገኙ ዜጎች በበኩላቸው፤ በዘርፉ በመሰማራታቸው ከዕለታዊ ፍጆታ ባለፈ ሌሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻላቸውን ይናገራሉ።

ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ሸምሱ ነጋሽ፤ ቀደም ሲል በሴፍቲኔት ፕሮግራም ተረጂ እንደነበሩ አስታውሰው፣ መንግሥት ባመቻቸላቸው ዕድል ወደ ከተማ ግብርና በመግባት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወይዘሮ መይሙና ጀማል በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ እንዳልነበራቸው አስታውሰው፤ አሁን በከተማ ግብርና ተሰማርተው ውጤታማ እየሆኑ መመጣታቸውን ተናግረዋል።


ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት ሽመልስ ድሪባ፤ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ከጓደኞቹ ጋር በመደራጀት ውጤታማ ሥራ እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

ከመንግሥት ባገኙት ብድር አምስት ላሞች ገዝተው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሶ በአሁኑ ወቅት የላሞቻቸው ቁጥር ከ20 በላይ መድረሱንና ለሌሎች ወጣቶችም የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ተናግሯል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们