登录以查看您的控制台资源

新闻通稿 SEO营销 媒体监测

联系我们

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት መጠናከር ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል

发布:5/12/2026 阅读:1

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2018(ኢዜአ)፦ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት መጠናከር ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ ገለጹ።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሥራ አፈፃጸም አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ፤ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ብለዋል።

ለዚህም ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ዕድገትን በማፋጠን በኩል ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ፈጣንና ጤናማ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ በኢንቨስትመንት መሳተፍ አስደሳች መሆኑን ጠቁመው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካች አዎንታዊ ውጤቶች ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ምቹ የልማት ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል።

በቴሌኮም ዘርፍም አበረታች የቁጥጥር ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸው፤ ይህም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞች ቁጥር 13 ነጥብ 6 ሚሊየን ማድረስ ማስቻሉን አስረድተዋል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ54 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን በመግለጽ።

የኤም-ፔሳ (M-PESA) ተጠቃሚዎች ቁጥር 5 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንና በመተግበሪያው የተደረገው የገንዘብ ዝውውርም 32 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መድረሱን አብራርተዋል።

የሞባይል ዳታ አገልግሎት በዓመታዊ ገቢ ላይ ትልቁን ድርሻ በመያዝ ጠንካራ ዕድገት ማሳየቱንም ጨምረው ጠቁመዋል።

በተጠናቀቀው የ2026 በጀት ዓመት 15 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንና ይህም የ130 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት እንዳለው አመላክተዋል።

传播你的梦想,是我的使命

精准触达,高效发声,让每一次发布都有回响,把专业的事,交给专业的人,助你专注核心,我们搞定传播。

微信扫一扫 立即联系我们